ዜና ዝርዝር

የሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

የሀገር ሀብት ወደ ካዝና ገብቶ ለሕዝብ ጥቅም መዋል ጀምሯል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Development

የሀገር ሀብት ወደ ካዝና ገብቶ ለሕዝብ ጥቅም መዋል ጀምሯል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

August 13, 2026 54 እይታዎች 01:33 PM

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለውን የኢኮኖሚ ዕድገት ከለውጡ በፊት ከነበረው የሀብት ብክነት ጋር በማነጻጸር መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚሁም ኢትዮጵያ በቅርቡ በወርቅ ወጪ ንግድ ላይ ያስመዘገበችውን ስኬት እንደ ማሳያ አንስተዋል።

ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ 5.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ወርቅ ወደ ውጭ ገበያ መላክ መቻሉን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ይህ አኃዝ ከለውጡ በፊት በነበሩት 27 ዓመታት ውስጥ ወደ ውጭ ከተላከው 3.6 ቢሊዮን ዶላር የላቀ መሆኑን አስምረውበታል።

ይህ እውነታ የሚያሳየው አዲስ ወርቅ ተገኝቶ ሳይሆን፣ ሀብቱ ቀድሞውንም ቢሆን በግለሰቦች ሲዘረፍ መቆየቱን ነው በማለት ሐሳባቸውን አጠናክረዋል።

ባለፉት ሥርዓቶች የሀገራችን ሀብት ለሀገር ልማት ከመዋል ይልቅ ግለሰቦች ፎቅ እንዲገነቡበት ሲደረግ መቆየቱን በማስታወስ፣ አሁን ግን ይህ ሀብት ወደ ሀገር ካዝና ገብቶ ለሕዝብ ጥቅም እየዋለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል።

የሰላም ጠላቶች ይህንን እውነት መቀበል ስለሚከብዳቸው እና የማይሻሻል አስተሳሰብ ስላላቸው ሀገራችንን ወደ ሁከት ለመክተት እንደሚሞክሩ አብራርተዋል።

ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት ውስጥ በዲፕሎማሲ፣ በግብርና እና በአዲስ አበባ ከተማ ልማት የተመዘገቡት ስኬቶች፣ ባለፉት 27 ዓመታት ከተሠራው በላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብም ጭምር የነበረውን እውነታ ተረድቶ ከትናንትናው አዲስ አስተሳሰብ እና የነቃ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ቀዳሚ ዜና ሁሉንም ዜናዎች ቀጣይ ዜና