የሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የቅርብ ጊዜ ዜናዎች
ሰኔ 11/2018 የሲዳማ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ
የፈተና መርሐ ግብር በተመለከተ በሀዋሳ ሐይቅ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ፈተና ያስጀመሩት የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ እንደገለጹት ተፈታኞችን ብቁ ለማድረግ በየደረጃው ዓመቱን ሙሉ የተለያዩ የትምህርት ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል ።ከዚህ በፊት በክልሉ ውስጥ ከአንድ ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ፈተና እንደሚሰጥ በማንሳት ዘንድሮ በተለየ ሁኔታ 232 ማዕከላት እየተሰጠ ያለ መሆኑን ነው ም/ርዕሰ መስተዳድሩ የገለፁት።
በ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 49 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱም ነው የገለፁት።
የፈተና ሂደቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብና በዕቅዱ መሠረት የሚከናወን ስሆን ተፈታኞችን ለማወክ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጭ ሀሰተኛ መረጃ ተማሪዎችና መላው ህብረተሰብ እንዲጠነቀቁና በዓላው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ም/ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ለበለጠ መረጃ
➚ድረ ገጽ፦ https://sidamanrsps.gov.et
➚ፌስቡክ፡- Sidama National Regional State Communication Affairs Bureau
➚ዩትዩብ፦https://youtube.com/@snrscom.bureau?si=r5EAWg8x4kXmLqQN
➚WhatsApp https://whatsapp.com/channel/0029VadMPA2DDmFbMwfTjG3l